ከአዋጭ ጋር መስራት ያኮራል” አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለሴቶችና ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡
 በሀገራችን የፋይናንስ ዘርፍ የላቀ ስም ያለው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ላለፉት ሁለት ዓመታት ከ “ምን አማረሽ” የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር የጀመረውን ውጤታማ አጋርነት በማጠናከር ሴቶችንና አርቲስቶችን ያሳተፈ ደማቅ የዕውቅና እና የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር አካሄደ።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአዋጭ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ አዋጭ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ለሴቶች የሚሰጠውን ትኩረት በማድነቅ “ከአዋጭ ጋር መስራት በእጅጉ ያኮራል” ስትል ስሜቷን ገልጻለች። በተመሳሳይ መልኩ አንጋፋው የቲያትር መምህር፣ አዘጋጅና ተዋናይ አርቲስት ተስፋዬ ሲማ አዋጭ ለአርቲስቶች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተምሳሌታዊ መሆኑን በመጥቀስ ተቋሙ ለዘርፉ እድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል።

የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ በበኩላቸው፣ ተቋሙ አባላቱን ከመደገፍ ባለፈ የብዙዎችን ህልም እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል። ለአባላቶቻችን የምናደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን፤ የእናንተን ህልም መደገፍ የሁልጊዜም ትጋታችን ነውም ብለዋል።
በዕለቱ ለተጋበዙ አርቲስት አባላትም ለአዋጭ እና ለዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዘሪሁን ሸለመ በዓለም አቀፍ ደረጃ (ICA Africa) ላስመዘገቡት ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ይህ መርሃ ግብር አዋጭ በሀገር ግንባታና በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድ ያለውን ሚና ዳግም ያረጋገጠበት ሆኖ ተጠናቋል።

Share

Recent News

ICA Africa Director Dr. Rose Karimi Leads Delegation on Visit to Awach SACCOS

ADDIS ABABA, October 28, 2026 – A high-level delegation led by Dr. Rose Karimi, Director…….

US-Based Associated Credit Union VP Hiwote Tadesse Visits Awach SACCOS, Leads Women’s Leadership Training

Addis Ababa, October 21, 2026 — Hiwote Tadesse, Chief Human Resources Officer and Vice President…….

Ceremony To Honor Heroic Mothers

On December 13, 2025 (Tahsas 4, 2018 E.C.), the Awach Foundation held a special ceremony…….

Be a Member