እንኳን ደስ አላችሁ፤ በአንድነት አሳክተነዋል! Baga Gammaddan Injifanneerra!

ውድ የአዋጭ አባላት፣ የኅብረት ሥራ ቤተሰቦችና መላው ኢትዮጵያውያን የአለም ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ ኅብረት (ICA – Africa) ባዘጋጀው የ2026 ታላቅ አህጉራዊ አዋርድ ላይ፥ የኢትዮጵያ ስም በኩራትና በክብር ናኝቷል።

በአፍሪካ የኅብረት ሥራ ዘርፍ «ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሪ» በመባል የኅብረት ሥራ ማኅበራችን መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ፤ እንዲሁም «በአፍሪካ ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኅብረት ሥራ ማኅበር» በመባል አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር ደምቀው በመውጣት ታላቁን አህጉራዊ ድል ተቀዳጅተዋል።
ኩራታችን የሆናችሁ የኅብረት ሥራ ማኅበራችን ቤተሰቦቻችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በአፍሪካ መድረክ ላይ ከፍ ብለን እንድንታይ፣ የሀገራችንን የኅብረት ሥራ ጥንካሬና ተወዳዳሪነት ለዓለም እንድናሳይ የሰጣችሁን እያንዳንዷ ድምፅ (Voting) የዚህ ድል መሠረት ናት። ያላችሁን ፍቅርና አጋርነት በምርጫው ዘመቻ ላይ በተግባር አሳይታችሁናልና ምስጋናችን እጥፍ ድርብ፣ ከልብም የላቀ ነው።

ኢትዮጵያ የኅብር ሀገር ናት። ትውልድ ዘወትር የሚዘክረውን ድል አድራጊነትና የአንድነት ኃይል ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ በተግባር ያሳየች ታሪካዊት ምድር። ይህ የመተባበር እምቅ አቅምና ክንድ በሰሞኑ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ በጉልህ ታይቷል፤ ቃላት ውለታችሁን ለመግለጽ ውስን ናቸውና በተግባር ለገለጻችሁት ታላቅ ፍቅርና አብሮነት ኅብረት ሥራ ማኅበራችን የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል።

Share

Recent News

ICA Africa Director Dr. Rose Karimi Leads Delegation on Visit to Awach SACCOS

ADDIS ABABA, October 28, 2026 – A high-level delegation led by Dr. Rose Karimi, Director…….

US-Based Associated Credit Union VP Hiwote Tadesse Visits Awach SACCOS, Leads Women’s Leadership Training

Addis Ababa, October 21, 2026 — Hiwote Tadesse, Chief Human Resources Officer and Vice President…….

Ceremony To Honor Heroic Mothers

On December 13, 2025 (Tahsas 4, 2018 E.C.), the Awach Foundation held a special ceremony…….

Be a Member