አዋጭ 15ኛ ዓመት ክብረ በአሉን አስመልክቶ ለተለያዩ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

 አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ስራ ማህበር የ15ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ማክሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለመጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በህብረት ሥራ ማህበሩ መስራችና እና ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ዘሪሁን ሸለመ አማካኝነት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡ በመግለጫውም ላይም ስለ ህብረት ሥራ ማህበሩ ምስረታ እንዲሁም ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ህብረት ስራ ማህበሩ ስላሳለፉቸው የጥረት እና የስኬት ጉዞዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር በአሁኑ ጊዜ ከ62,522 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ባለፉት አስራ አምስት አመታት ውስጥ ከ30 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በተሰጠው 2.8 ቢሊዮን ብር ብድር አማካኝነት የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ቤላ ለሚገኘው የመከላከያ ማገገሚያ ሆስፒታል ድጋፍ ለማድረግ በዝግጀት ላይ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome