አዋጭ ታህሳስ 15ቀን 2015ዓ.ም 19ኛ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤውን በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል አካሄደ፡፡

አዋጭ ታህሳስ 15ቀን 2015ዓ.ም 19ኛ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤውን በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል አካሄደ፡፡

አዋጭ በ19ኛ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤው የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2013/14 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ አባላት የፀደቀ ሲሆን የኦዲት ሪፖርቱም 100⁒ በሚባል መልኩ ነጻ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ መከናወኑን እንዲሁም በባለፈው በጀት ዓመት (ከሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም) የስራ አፈጻጸም በአጠቃላይ 205,756,840.85 ዓመታዊ ትርፍ ማስመዘገቡን የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን  ኦዲተሮች ለጉባዔው ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2013/14 በጀት ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል 25.2 ⁒ መሆኑ ተገልጾ ለአባላቱ እንዲከፋፈል በህብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ፀድቋል፡፡ በተጨማሪም አዋጭ ካተረፈው ዓመታዊ ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆነው ለህብረት ስራ ማህበሩ መጠባበቂያ ተቀማጭ የሚሆን ሲሆን ከመጠባበቂያ ተቀማጭ ውጪ ከሆነው 70 በመቶ ትርፍ ውስጥ 5⁒ የሚሆነውን ለማህበራዊ አስተዋጽዖ እንዲውል ጉባኤው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome