አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሠ የኅብረት ሥራ ማህበር ለ3 ተከታታይ ቀናት ስልጠናና ውይይት አካሄደ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሠ የኅብረት ሥራ ማህበር እየተጓዘ ላለበት ፈጣን እድገት ይህን መሰሉ ስልጠና እና ውይይት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ብሎም ወደፊት ለሚገጥሙት ማንኛውም ተግዳሮቶች ለመቋቋም የሚያስችል የተሻለ አቅም ይፈጥርለታል

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሠ የኅብረት ሥራ ማህበር ለ3 ተከታታይ ቀናት ለየክፍሉ የስራ ኃላፊዎች ስለ ኅብረት ስራ ማህበራት ፅንሰ ሃሳብ ፣ የኅብረት ስራ ማህበሩ በሚቀጥሉት ጊዜያት ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መከላከል በሚችልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና እንዲሁም ለሚቀጥሉት 5 አመታት የኅብረት ሥራ ማህበሩ ለሚመራበት ስራቴጂክ ፕላን ግብዓት የሚሆኑ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡ ስብሰባውን መርቀው የከፈቱት የፌደራል የኅብረት ሥራ ማህበራት ኤጀንሲ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ዱፌራ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሠ የኅብረት ሥራ ማህበር እየተጓዘ ላለበት ፈጣን እድገት ይህን መሰሉ ስልጠና እና ውይይት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ብሎም ወደፊት ለሚገጥሙት ማንኛውም ተግዳሮቶች ለመቋቋም የሚያስችል የተሻለ አቅም ይፈጥርለታል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome