ቁጠባ

አንድ አባል ለቆጠበው ቁጠባ በዓመት 7 በመቶ የተቀማጭ ወለድ ይታሰብለታል፡፡

መደበኛ ቁጠባ

ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል የሆነ የማህበሩን መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 ወይም የ30 ቀናት ገቢው ውስጥ 10 በመቶውን ሳያቋርጥ በየወሩ መቶጠብ ይኖርበታል፡፡ አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው፡፡

የፍላጎት ቁጠባ     

አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል፡፡ ይህንንም ቁጠባ በማንኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡

የቤት ቁጠባ

አንድ አባል ቤት ለመግዛት፣ ለመስራት ወይም ለማደስ  የቤት ብድር መውሰድ ቢፈልግ ለአንድ ዓመት በተከታታይ ሳያቋርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 25 በመቶ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ 

የቤት መኪና ቁጠባ

አንድ አባል የቤት መኪና ለመግዛት የመኪና ብድር መውሰድ ቢፈልግ ለአንድ ዓመት በተከታታይ ሳያቋርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 25 በመቶ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

የትራንስፖርት መኪና ቁጠባ

አንድ አባል የትራንስፖርት መኪና ለመግዛት የመኪና ብድር መውሰድ ቢፈልግ ለአንድ ዓመት በተከታታይ ሳያቋርጥ የሚወስደውን ብድር 25 በመቶ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ 

ቁጠባ ወለድ

አንድ አባል ለቆጠበው ቁጠባ በዓመት 7 በመቶ የተቀማጭ ወለድ ይታሰብለታል፡፡ 

የህፃናት ቁጠባ

የማኅበረሰቡ የመቆጠብ ልምድ እንዲያድግ ማንኛውም ሰው በህብረት ሥራ ማህበር ውስጥ መግባት እና ልጆቻቸውንም አባል እንዲያደርጉ ያመቻቻል 

የአነስተኛ ንግድ ቁጠ

አንድ አባል አነስተኛ ንግድ ለመጀመርም ሆነ ለማስፋፋት ቢፈልግ ለስድስት ወር በተከታታይ ሳያቆርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 30 በመቶ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome