
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር ህብረተሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ እራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በአቶ ዘሪሁን ሸለመ ዋና መስራችነት 41 አባላትን በማሰባሰብ መጋቢት 13 ቀን 1999 ዓ.ም. በመጀመሪያ በአራዳ ክፍለ ከተማ አዋጅ 147/91 ተመሰረተ፡፡ ኅብረት ሥ ማኅበሩ ባሳየው ከፍተኛ እድገት የሥራ ክልሉን በማስፋት በፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጅንሲ ምዝገባ ቁጥር አገ/ቁ/ብ/005/09 ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው፣ በፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ብቃት ማረጋገጫ መመሪያ ቁጥር 018/2007 መሠረት ተመዝኖ 81.65 ከመቶ በማግኘት በከፍተኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ታህሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. የተሰጠው ኅ/ሥ/ማኅበር ነው፡፡ በተጨማሪም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ኅብረት ሥራ ኅብረት (International Cooperative Alliance) አባል እንዲሁም የአፍሪካ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ኮንፌደሬሽን (African Confederation Saving & Credit Cooperative Association) ተባባሪ አባል የሆነ ማኅበረሰብ አቀፍ የህብረት ሥራ ማኅበር ነው፡፡