አገልግሎቶች

ቁጠባ
መደበኛ ቁጠባ ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል የሆነ የማህበሩን መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 ወይም የ30 ቀናት ገቢው ውስጥ 10 በመቶውን ሳያቋርጥ በየወሩ መቶጠብ ይኖርበታል፡፡ አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው፡፡ የፍላጎት ቁጠባ      አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል፡፡ ይህንንም ቁጠባ በማንኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡ የቤት ቁጠባ አንድ አባል ቤት ለመግዛት፣ ለመስራት ወይም ለማደስ የቤት ብድር መውሰድ ቢፈልግ ለስድስት ወራት በተከታታይ ሳያቋርጥ የሚወስደውን ብድር መጠን 25 በመቶ መቆጠብ…
loan -money-exchange-currency-business and finance-hand
ብድር
የብድር አገልግሎት አዋጭ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የብድር አገልግሎት ነው፡፡ ማንኛውም አባል ለብድር የሚጠየቁ ቅድመ መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ብድር የማግኘት መብት አለው፡፡ ለዚህም  የህብረት ስራ ማህበሩ የብድር ኮሚቴ እና የብድር ክፍል አንድ አባል ብድር እንዲወስድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ቅድመ ሁኔታውን ያሟሉ አባላት የሚያቀርቡት የብድር ማመልከቻዎችን የብድር ክፍል በማየትና በማረጋገጥ ለብድር ኮሚቴ አፀድቆ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማቅረብ ክፍያ እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡  የብድር መስፈርቶች አንድ ለመበደር ያሰበ አባል አባል ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ…
የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
አዋጭ ለአባላቱ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ይሰጣል ከነዚህም ውስጥ የኅብረት ሥራ ማህበር ታሪካዊ አመጣጥ፣ የአዋጭ እድገት፣ የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የንግድ ክህሎት ናቸው ::
© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome