ዜና

የግል እና የንግድ ግቦችዎን ለማሳካት እንዲረዱዎት ታስበው የተዘጋጁ፣ ተወዳዳሪ እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ያላቸውን ብድሮች ያግኙ።

እንኳን ደስ አላችሁ፤ በአንድነት አሳክተነዋል! Baga Gammaddan Injifanneerra!

ውድ የአዋጭ አባላት፣ የኅብረት ሥራ ቤተሰቦችና መላው ኢትዮጵያውያን የአለም ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ ኅብረት (ICA – Africa) ባዘጋጀው የ2026 ታላቅ አህጉራዊ አዋርድ ላይ፥ የኢትዮጵያ ስም በኩራትና በክብር ናኝቷል።

በአፍሪካ የኅብረት ሥራ ዘርፍ «ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሪ» በመባል የኅብረት ሥራ ማኅበራችን መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ፤ እንዲሁም «በአፍሪካ ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኅብረት ሥራ ማኅበር» በመባል አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር ደምቀው በመውጣት ታላቁን አህጉራዊ ድል ተቀዳጅተዋል።
ኩራታችን የሆናችሁ የኅብረት ሥራ ማኅበራችን ቤተሰቦቻችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በአፍሪካ መድረክ ላይ ከፍ ብለን እንድንታይ፣ የሀገራችንን የኅብረት ሥራ ጥንካሬና ተወዳዳሪነት ለዓለም እንድናሳይ የሰጣችሁን እያንዳንዷ ድምፅ (Voting) የዚህ ድል መሠረት ናት። ያላችሁን ፍቅርና አጋርነት በምርጫው ዘመቻ ላይ በተግባር አሳይታችሁናልና ምስጋናችን እጥፍ ድርብ፣ ከልብም የላቀ ነው።

ኢትዮጵያ የኅብር ሀገር ናት። ትውልድ ዘወትር የሚዘክረውን ድል አድራጊነትና የአንድነት ኃይል ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ በተግባር ያሳየች ታሪካዊት ምድር። ይህ የመተባበር እምቅ አቅምና ክንድ በሰሞኑ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ በጉልህ ታይቷል፤ ቃላት ውለታችሁን ለመግለጽ ውስን ናቸውና በተግባር ለገለጻችሁት ታላቅ ፍቅርና አብሮነት ኅብረት ሥራ ማኅበራችን የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል።

ያጋሩ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

እንኳን ደስ አላችሁ፤ በአንድነት አሳክተነዋል! Baga Gammaddan Injifanneerra!

ውድ የአዋጭ አባላት፣ የኅብረት ሥራ ቤተሰቦችና መላው ኢትዮጵያውያን የአለም ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ ኅብረት (ICA…….

ከአዋጭ ጋር መስራት ያኮራል” አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለሴቶችና ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል…….

Be a Member