ስለ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር ህብረተሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በአቶ ዘሪሁን ሸለመ ዋና መስራችነት 41 አባላትን በማሰባሰብ መጋቢት 13 ቀን 1999 . በአራዳ ክፍለ ከተማ አዋጅ 147/91 ተመሰረተ፡፡ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ባሳየው ከፍተኛ እድገት የሥራ ክልሉን በማስፋት በፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ምዝገባ ቁጥር አገ///005/09 ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው፣ በፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ብቃት ማረጋገጫ መመሪያ ቁጥር 018/2007 መሠረት ተመዝኖ 91.09 ከመቶ በማግኘት በከፍተኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰኔ 7 ቀን 2013 .. የተሰጠው ኅ//ማኅበር ነው፡፡ በተጨማሪም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ኅብረት ሥራ ኅብረት (International Cooperative Alliance) አባልና የአፍሪካ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ኮንፌደሬሽን (African Confederation Saving & Credit Cooperative Association) ተባባሪ አባል የሆነ ማኅበረሰብ አቀፍ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው፡፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome