ወ/ሪት ማህሌት መስፍን

From
Addis Ababa
አዋጭ ለዋጭ ነው!!!

ማህሌት መስፍን እባላለሁ፡፡ የአዋጭየገ///ሀላ/የተ/የህ//ማህበር አባል የሆንኩት በወንድሜ በሄኖክ መኮንን ምክንያት ነው፡፡ ለመበደር መቆጠብ እንዳለብኝ ሲነግረኝ እና እሱ ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ገብቶ ያገኘውን ጥቅም ስለተረዳሁ በ 20/04/2006 .ም በደብተር ቁጥር 1433 የቁጠባ ደብተር በማውጣት እኔም አባል ልሆን ችያለሁ፡፡ አዋጭ ከመግባቴ በፊት የኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ውስጥ ተቀጥሬ ነበር የምሰራው፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ኒያላ ኢንሹራንስ ውስጥ ተቀጥሬ እሰራለሁ፡፡ አዋጭ ከመግባቴ በፊት የትም ቦታ ቁጠባ ቆጥቤ አላውቅም፡፡ ገንዘብ ለመቆጠብ ብዬ የባንክ ቡክ አውጥቼ አላውቅም መስሪያ ቤቴ ነው ለደሞዝ ሲባል የባንክ ደብተር እንዳወጣ ያረጉኝ፡፡ ነገር ግን እዛ ላይ ምንም ገንዘብ አላስቀምጥም ፡፡ ገንዘቡን እንዳለ አውጥቼ እጠቀምበታለሁ፡፡ አዋጭ ገንዘብ ማስቀመጥ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እንድረዳ አድርጎኛል፡፡ አሁን ላይ ያለኝን ብር ጠቅልዬ አውጥቼ አላጠፋም፡፡አዋጭ ያለ ጥቅም እና ያለአግባብ ገንዘብ ማውጣት እንደሌለብኝ አስተምሮኛል፡፡ገንዘብ እንኳን ስፈልግ ከሰው ከመበደር ይልቅ ከህብረት ስራ ማህበሬ መውሰድ እንደምችል እና በየትኛውም የችግሬ ሰዓት ላይ ካሽ በእጄ እንዳለ እንድተማመን አድርጎኛል፡፡

የመጀመሪያ ዙር ብድር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ) ብር ነበር የወሰድኩት፡፡ በወቅቱ ብድሩን የወሰድኩት ማስተርሴን ለመማር ነበር፡፡ ለመማር ደግሞ የትምህርት ቤት ክፍያን ጨምሮ የተለያዩ ወጪዎች አሉ፡፡ በተለይ በየሴሚስተሩ የሚከፈል የትምህርት ቤት ክፍያ ለመክፈል መጨናነቅ አልፈለኩኝም፡፡ ለሚቀጥለው ሴሚስተር ላይ ከየት አምጥቼ እከፍላለሁ ብዬ ማሰብ ስላልፈለኩ ከህብረት ስራ ማህበሬ ብድር ወሰድኩኝ፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ ዙር የወሰድኩት ብድር ብቻውን ትምህርቴን ለመጨረስ አልበቃኝም ፡፡ ስለዚህ ሁለተኛ ዙር ብድር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ብር ወስጄ ትምህርቴን ቀጠልኩ ማለት ነው ፡፡ ያው መጪው ወር ላይ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከቅድስተማሪያም ዩኒቨርሲቲ እመረቃለሁ ፡፡ አዋጭ ትምህርቴን ሳልጨናነቅ በትክክል እንድማር አድርጎኛል፡፡

አዋጭ ከገባሁ በሁዋላ የቁጠባ ባህሌን አሳድጌያሁ ፣ በኔ የተነሳ ሁለቱ ጓደኞቼ መግባት ችለዋል፡፡ የእነሱን ቁጠባ ላይ ያላቸውን አመለካከት መቀየር እራሱ ለኔ በጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡ ባይኖራቸውም እንኳን ካላቸው ላይ መቆጠብ እንደሚችሉ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚያስቡት በማስቀመጥ ውስጥ መቋጠር ወይም ደግሞ ለራስህ ብቻ አድልቶ ሌሎችን መጉዳት ሳይሆን ሁሉንም ነገር አመጣጥኖ መሄድ እንደሚቻል ለሌሎች ማሳመን ችያለሁ ፡፡እኔ በግሌ ለጓደኞቼ ይህንን አሳይቻለሁ ብያለሁ ይሄ ደግሞ ለኔ ሶስተኛ ጥቅሜ ነው፡፡

ወደፊት ትምህርቴን ከጨረስኩ በኌላ የማላውቀው የራሴን ስራ ለመስራት አቅጃለሁ፡፡ አሁን ላይ ልክ ቅጥር ያስረጀው ሰው አይነት ሆኛለሁ እስካሁን በስራ አለም ላይ አምስት አመት ሊሆነኝ ነው፡፡ ቅጥር የሚበቃኝ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ የሚቀጥለው መንገዴ ትንሽም ቢሆን የራሴ የሆነ ነገር እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፡፡ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ስቀጠር ልጅነትም ስለነበረ በመስራቴ ብቻ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ሌላ ጥያቄ ውስጤ አያነሳም ነበር፡፡ ስለዚህ አዋጭ የራሴን ነገር እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ አዋጭ ለዋጭ ነው፡፡ ብዙ የሚለውጥ ነው፡፡ ለዋጭ ሲባል ብዙ ነገር አለ፡፡ በአስተሳሰብም ሊለውጥ ይችላል፡፡ እንዲሁም ከአላማ አንፃር ውጤታማ ያደርጋል፡፡ እግዜር ይስጥልኝ፡፡

© Awach SACCoS. All rights reserved
Website By: Alen Teshome